
ደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
Debre Tibeb Beata LeMariam Ethiopian Orthodox Tewahedo Church (DTBLM-EOTC) diocese of Washington, Oregon, Idaho and surrounding areas of North America
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ኦሪገን አይዳሆና አካባቢው አህጉረ ስብከት የደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
"ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ፤” (መዝ. ፵፬፥፲፪)
ብዙዎች ቅዱሳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው እጅግ አስደናቂ ውበቷን አይተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በደብረ ምጥማቅ የነበሩ ምእመናን ሌሎችም ብዙዎች ንጹሓን ክርስቲያኖች ይገኙበታል፡፡
እኛንም ድንግል ማርያም ትባርከን በኑሮአችን በሕይወታችን በስራችን በልጆቻችን በትዳራችን በረድኤት በበረከት በቸርነት ትገለጥልን፡፡ አሜን፡፡

